ለዓለም ከ20 ዓመት በታች የሴቶች እግር ኳስ ኢትዮጵያ በመጪው እሁድ ኬንያን ትገጥማለች

በ2018 በፈረንሳይ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአለም ከ20 ዓመት በታች የሴቶች የእግር ኳስ ዋንጫ የመጀመሪያ ዙር የማጣሪያ ውድድር ኢትዮጵያ በመጪው እሁድ ሀዋሳ ላይ ኬንያን ትገጥማለች።

የኢትዮጵያ ሴቶች ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከነሐሴ አጋማሽ ጀምሮ በሀዋሳ ልምምዳቸውን ሲያደርጉ ቆይቷል።

የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ቴዎድሮስ ደስታ፥ በሜዳችንና በደጋፊያችን ፊት የምናደርገውን ጨዋታ ማሸነፍ የሚያስችል ልምምድ አድርገናል ሲል ተናግሯል።

''ለዚህም ይረዳኝ ዘንድ የመሀል ሜዳ ንክኪዎችን ሳይሆን በፍጥነት ወደ ጎል ለመድረስ የሚጠቅመኝን አጨዋወት እከተላለሁ'' ያለው አሰልጣኝ ቴዎድሮስ የስፖርት ቤተሰቡ ቡድኑን እንዲደግፍ ጥሪውን አስተላልፏል።

የብሄራዊ ቡድኑ ተጫዋቾች፣ አሰልጣኞች እና ፌደሬሽኑ የሚችሉትን ድጋፍ እንዳደረጉላቸውና በአግባቡ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

የብሔራዊ ቡድኑ አምበል ዘይነባ ሰይድ በቡድኑ ውስጥ በአሰልጣኙም ሆነ በተጫዋቾች መካከል ያለው ግንኙነት ጥሩ እንደሆነ ተናግራለች።
በተለይ አሰልጣኞች ለተጫዋቾች ባላቸው አክብሮት ደስተኛ መሆኗን ገልፃለች።

ብዙዎቹ ተጫዋቾች ከእረፍት በመመለሳቸው የአካል ብቃታቸው ዝቅተኛ ስለነበር ክፍተቱን ለመድፈን በሚገባ መዘጋጀታቸውን ተናግራለች።

ተጫዋቹም ሆነ አሰልጣኙ በዚህ ጨዋታ ህዝቡ ሜዳ ገብቶ ድጋፉን እንዲሰጣቸውና እንዲያበረታታቸው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ሴቶች ከ20 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን የመልሱን ጨዋታ ከሁለት ሳምንት በኋላ በኬኒያ የሚያደርግ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በደርሶ መልስ የኬንያ አቻውን ካሸነፈ በሁለተኛው ዙር ማጣሪያ ከአልጀሪያ እና ጋና አሸናፊ ቡድኖች ጋር የሚጫወት ይሆናል።

ምንጭ፦ ኢዜአ

Share this post

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to StumbleuponSubmit to TechnoratiSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Rate this item
(0 votes)

37830 comments

Leave a comment

Make sure you enter all the required information, indicated by an asterisk (*). HTML code is not allowed.

Information for All

Go to top